
abenet agonafer - baybay lyrics
ምንም የለም ቅር የሚለኝ
ሁሉን ነገር ስላልደበቅሽኝ
እያወኩኝ መከፋቴ
አሳስቦኝ ነው ብቸኝነቴ
ተደስቼ እንድታይኝ
ሞክሬያለሁ ግን እምቢ አለኝ
ለኔ ብለሽ ተይ አታኩርፊ
በደስታሽ ቀን አትከፊ
ደስታሽማ ደስታዬ ነው
የቃተኝ መለየቱ ነው (ባይ ባይ ባይ)
ቀን ሲቆረጥ ለመንገድሽ
መሰለኝ የማላገኝሽ (ባይ ባይ ባይ ባይ ባይ)
ይሳካል ይሆናል አይዞሽ
እንዳላልኩ ሆኜ ከጎንሽ (ባይ ባይ ባይ)
ፍቅራችን እያሳሰበኝ
በድንገት ነው ሆድ የባሰኝ (ባይ ባይ ባይ ባይ ባይ)
እንዲሁ እንዳላችሁ አይለያችሁ ያሉን
ብቻዬን ያዩኝ ቀን ምን ይሆን ሰው ሚለን
ተራርቆ ፍቅር ይከብዳል ወዳጄ
እንዴት ነው ምለምደው ወድጄም ፈቅጄ
(ባይ ባይ) ደህና ሁን አትበይኝ
(ባይ ባይ) አትበይኝ ፈራለው
(ባይ ባይ) ወተሽ እስክትገቢስ
(ባይ ባይ) መቼ እኔ ችላለው
(ባይ ባይ) ደህና ሁን አትበይኝ
(ባይ ባይ) አትበይኝ ፈራለው
(ባይ ባይ) ስትመጪ ማቆማው
(ባይ ባይ) ቀኑን እቆጥራለው
(ባይ ባይ) ደህና ሁን አትበይኝ
(ባይ ባይ) አትበይኝ ፈራለው
(ባይ ባይ) ልብሽን ተይልኝ
(ባይ ባይ) ስወድሽ ኖራለሁ
ምንም የለም ቅር የሚለኝ
ሁሉን ነገር ስላልደበቅሽኝ
እያወኩኝ መከፋቴ
አሳስቦኝ ነው ብቸኝነቴ
ተደስቼ እንድታይኝ
ሞክሬያለሁ ግን እምቢ አለኝ
ለኔ ብለሽ ተይ አታኩርፊ
በደስታሽ ቀን አትከፊ
በይ ስሚኝ እህ በይና
ሴት መሆን አለው ፈተና (ባይ ባይ ባይ)
መንገዱን እንጂ ማያውቀው
ሰው ሲሄድ ሸኚው ብዙ ነው (ባይ ባይ ባይ ባይ ባይ)
በሰላም ተመለሽልኝ
ጨርሰሽ እንዳትለይኝ (ባይ ባይ ባይ)
መጥቼ ግን አልሸኝሽም
ሆድሽን አላባባሽም (ባይ ባይ ባይ ባይ ባይ)
እንዲሁ እንዳላችሁ አይለያችሁ ያሉን
ብቻዬን ያዩኝ ቀን ምን ይሆን ሰው ሚለን
ፍርሃቴን ደስታዬን ፍቅሬን ብነግርሽም
እንዲቀለኝ ብዬ በእምባዬ አልሸኝሽም
(ባይ ባይ) ደህና ሁን አትበይኝ
(ባይ ባይ) አትበይኝ ፈራለው
(ባይ ባይ) ወተሽ እስክትገቢስ
(ባይ ባይ) መቼ እኔ ችላለው
(ባይ ባይ) ደህና ሁን አትበይኝ
(ባይ ባይ) አትበይኝ ፈራለው
(ባይ ባይ) ስትመጪ ማቆማው
(ባይ ባይ) ቀኑን እቆጥራለው
(ባይ ባይ) ደህና ሁን አትበይኝ
(ባይ ባይ) አትበይኝ ፈራለው
(ባይ ባይ) ልብሽን ተይልኝ
(ባይ ባይ) ስወድሽ ኖራለሁ
Random Lyrics
- 404vincent - check it out lyrics
- mbeyeline - got so many lyrics
- r. stevie moore - steve threw up lyrics
- paifan (grc) - κάπου θα με (kapou tha me) lyrics
- yunk vino - fetti lyrics
- krispylife kidd - intro 3 peat lyrics
- üm & tisha - human lyrics
- phillip phillips - dancing with your shadows lyrics
- pjonteczek - przywykłaś do "kocham cię" lyrics
- mvp productions - noodlemunch lyrics