ap est - gize/ጊዜ lyrics
[chorus + ap est]
ያኔ ሳለው ልጅ አንድ ዛፍ ነበር ከዛ ደጅ
ያሳደጉት ኮትኩተው እንደአባታቸው ልጅ
እርሱም ሰጣቸው ህይወት ቅንጣት ታህል ሳይሰለች
ጊዜው ሲያልፍ ሲያበቃ ቆረጡትም ሲያረጅ እኔም ተማርኩ
uhhhh yeah, ጊዜ ነው መጥፎ ጊዜ ነው ክፋ
uhhhh yeah, ከአቅም በላይ መውጣት መውደቅ ነው ትርፋ
uhhhh yeah, ዛሬ የተለቀ አይቀር ማነሱ
uhhhh yeah, ለሁሉም ጊዜ አለው ይህ ነው እውነቱ
[verse + pxf]
ጊዜ ነው ፈራጅ ጊዜ ነው መርማሪው
ትለፍም ትወድቅ ጊዜ ነው ነጋሪው
ያኔ ሲከፋኝ ወደአንተ ስመጣ
ትለኝ ነበር ያልፋል ይሄም በርታ
ለነገ ፈተና ይሆናል እርዳታ
ሂድ ወደፊት አታጣም ተስፋ
የልፋታችን መልስ ሳይጎድል ሙሉ ነው
ገና እንጥራለን መንገዱም እሩቅ ነው
ለሁሉም ጊዜ አለዉ እውነቱ ይኸው ነው
አጋምሰን መተናል መንገዱም እሩብ ነው
ካለው ላይ ወስዶ ለሌለው ቢሰጥ
ጥፋትስ ይባላል ንገረኝ በእውነት
በጊዜው የቆመ በጊዜው ይወድቅ
ዳሩ ግን መጠበቅ ሳይጠፋ እምነት
ዛሬ የቆመ ነገ አይቀርም መውደቁ
ታሪክ ላይ ቁም ነገሩ ሳንሰስት መስጠቱ
ችግሩ ቢበዛ ሀዘኑ ቢደረብ
አንድ ላይ ሆነን በርትተን ማለፉ
[chorus + ap est]
ያኔ ሳለው ልጅ አንድ ዛፍ ነበር ከዛ ደጅ
ያሳደጉት ኮትኩተው እንደአባታቸው ልጅ
እርሱም ሰጣቸው ህይወት ቅንጣት ታህል ሳይሰለች
ጊዜው ሲያልፍ ሲያበቃ ቆረጡትም ሲያረጅ እኔም ተማርኩ
uhhhh yeah, ጊዜ ነው መጥፎ ጊዜ ነው ክፋ
uhhhh yeah, ከአቅም በላይ መውጣት መውደቅ ነው ትርፋ
uhhhh yeah, ዛሬ የተለቀ አይቀር ማነሱ
uhhhh yeah, ለሁሉም ጊዜ አለው ይህ ነው እውነቱ
Random Lyrics
- kankan - sport lyrics
- olvi - abh lyrics
- hiimjulian - weißwein lyrics
- james giles - no one but you lyrics
- пика (pika) - парадайз (paradies) lyrics
- dunn d - time will tell lyrics
- dú maroc - szenario lyrics
- qwerty squad - flashback 2.0 lyrics
- h.s. - come back better lyrics
- pop evil - unstoppable lyrics