eyob mekonnen - man ende kal (ማን እንደ ቃል) lyrics
ውል አይፃፍ
ከኛስ ደጃፍ
ቅንጣት ላይተርፍ
ፍቅር ቢቀር ቢከንፍ
ልብ ይበቃል
መቆም ለቃል
ቤት ይሞቃል
በቃል በቃል በቃል
ወረቀት ምን ሊያድን
ፍቅር ቢሆን በድን
ንገሪኝ አምናለው
ቃልሽን አከብራለው
ውል አይፃፍ
ከኛስ ደጃፍ
ቅንጣት ላይተርፍ
ፍቅር ቢቀር ቢከንፍ
ልብ ይበቃል
መቆም ለቃል
ቤት ይሞቃል
በቃል በቃል በቃል
ወረቀት ምን ሊያድን
ፍቅር ቢሆን በድን
ንገሪኝ አምናለው
ቃልሽን አከብራለው
ልቤ ማን ገፍቶት አንቺን አለ
ያኔ ሳያምንበት መች ማለ
በህልሜም በእውኔም ካንቺው ጋራ ነኝ
ለዓይኔ ሌላ ዓለም መች አማረኝ
ፍቅሬን በወረቀት መች ፃፍሽው
እግሬን በፍቅርሽ ነው ያሰርሽው
ነፍሴ አካሌ ነሽ የጎኔ
ዶሴ ከኔ በላይ ለምኔ
ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግጦ
ሞላልኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴ ፍቅርሽ ነው ውስጤ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ
ውል አይፃፍ
ከኛስ ደጃፍ
ቅንጣት ላይተርፍ
ፍቅር ቢቀር ቢከንፍ
ልብ ይበቃል
መቆም ለቃል
ቤት ይሞቃል
በቃል በቃል በቃል
ወረቀት ምን ሊያድን
ፍቅር ቢሆን በድን
ንገሪኝ አምናለው
ቃልሽን አከብራለው
የእውነት የፍቅር ፅዋ በለስ
አምኖ ሳያምንበት የማይደርስ
መጣው ብዬ ቆሜ ከደጅሽ
ላድር ነው አንቺ ውስጥ በልብሽ
ስጋት የሌለው የተቃና
ለኛ ፍቅራችን ዋስ አለና
የኔ የምለውም ያንቺው ነው
ሌላው ምስክር የማያየው
ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግጦ
ሞላልኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴ ፍቅርሽ ነው ውስጤ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ
ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግጦ
ሞላልኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴ ፍቅርሽ ነው ውስጤ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ
ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግጦ
ሞላልኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴ ፍቅርሽ ነው ውስጤ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ
Random Lyrics
- anbar - memories lyrics
- artur karton - maryana raw lyrics
- boiw1der - diy lyrics
- mroku - zły mikołaj lyrics
- nora music - soñadora lyrics
- zt5 - marsiglia (la règle) lyrics
- lepa brena - sve smo mi krive lyrics
- devilish playa - concept killa lyrics
- lincon david - seja para deus lyrics
- madame monsieur - emmêler nos solitudes lyrics