azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

eyob mekonnen - wede enate bet lyrics

Loading...

እንደው ሙሉ ሆኜ ተፈጥሬ
በቀቢፀ ተስፋ ታጥሬ
ያጣሁ የሌለኝ

ደርሶ ቢመስለኝ
አወይ እግሬ
አወይ እግሬ
ወስዶ አወጣኝ ከሀገሬ
እንደው ሙሉ ሆኜ ተፈጥሬ
በቀቢፀ ተስፋ ታጥሬ
ያጣሁ የሌለኝ
ደርሶ ቢመስለኝ
አወይ እግሬ
አወይ እግሬ
ወስዶ አወጣኝ ከሀገሬ
ንፁህ ፍቅር እምነት ሰላም ሳይጠፋ
ነገን የሚያኖር ተስፋ
ሁሉ ሞልቶ ሳለ ከሀገር መንደሬ
ስስት ከማታውቅ ምድሬ
ልቤ ሩቅ ተመኘ በሰማው ተረቶ
ንቆ የራሱን ትቶ
ያሉት ከንቱ ቢያየው
ቀርቦ ቢረዳ
ሆነበት የህሊና እዳ (ኡህ)
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት በቃ እሄዳለዉ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው
እንደው ሙሉ ሆኜ ተፈጥሬ

በቀቢፀ ተስፋ ታጥሬ
ያጣሁ የሌለኝ
ደርሶ ቢመስለኝ
አወይ እግሬ
አወይ እግሬ
ወስዶ አወጣኝ ከሀገሬ
በአእዋፍ አፍ ወድቆ ተዘርቶ አብቦ
ሳይለፋ መብላት ጠግቦ
ሰፊ ውድ እርስቱን የአምላኩን ፀጋ
ክብሩን ነስቶት ዋጋ
ስደት ባዶ ቅዠት ወስዶኝ ከሀገሬ
ብስሉ ሊሆን ጥሬ
ላከስ አያምርብኝ ደስታም ሃዘኔ
የለሀገር ስኖር እኔ
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት በቃ እሄዳለዉ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት በቃ እሄዳለዉ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከ ሞቀ እቅፏ ልኑር ብያለው



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...