hewan gebrewold - yamral lju lyrics
Loading...
ያምራል ያምራል ያምራል ልጁ
ሁሉ በእጁ ነው በደጁ
ያምራል ያምራል ያምራል ምቱ
ዜማው ስልቱ የአውዳመቱ
ዳማይ ልጅ ዳማይ ዳማይ
የዛሬ አትውልም ወይ
ስመኝህ ኖሬ እንዳው ስመኝ
በአመት በአል አገጣጠመኝ
♪
ያለውም የሌለው በአቅሙ በደገሰው
ያምራል ሲሰባሰብ ወዳጅ የከርሞ ሰው
እጥፍ ድርብ ሀሴት ፍቅር የደስ ደስ
ይደራል ይጎዝጎዝ ጠጅ ሳር እና አደስ
እንኳንስ አንድ ላይ በስስት ላደገ
ልዩ ቀን ነው ዛሬ እርቅ ለፈለገ
እንኳን አደረሰን ለዚች ቀን በጤና
አያጉድል አይለየን ለአመቱ እንደገና
ያውዳመቱ ያውዳመቱ ያውዳመቱ
ይሄ ነው ውበቱ
ያገር ልጅ ያገር ልጅ ያገር ልጅ
ነው የማር ጠጅ
♪
ዳማይ ልጅ ዳማይ ዳማይ
የዛሬን አትውልም ወይ
ስመኝህ ኖሬ እንዳው ስመኝ
በአመት በአል አገጣጠመኝ
ብርቅ የከንፈር ወዳጅ የሩቅ መስሎ እንግዳ
ጠሪ አክባሪ እያለ ሲዘልቅ ወደ ጓዳ
ከፍሪዳው በላይ ወይ ከዶሮው ፋንታ
ፍቅርን ያደረጃል የአመት በአል ጨዋታ
እንኳንስ አንድ ላይ በስስት ላደገ
ልዩ ቀን ነው ዛሬ እርቅ ለፈለገ
እንኳን አደረሰን ለዚች ቀን በጤና
አያጉድል አይለየን ለአመቱ እንደገና
ያውዳመቱ ያውዳመቱ ያውዳመቱ
ይሄ ነው ውበቱ
ያገር ልጅ ያገር ልጅ ያገር ልጅ
ነው የማር ጠጅ
ዳማይ ልጅ ዳማይ ዳማይ
የዛሬ አትውልም ወይ
ስመኝህ ኖሬ እንዳው ስመኝ
በአመት በአል አገጣጠመኝ
Random Lyrics
- yung delirious - i ain't left yet lyrics
- p.h.f. - this is why we don't hang out lyrics
- tays [nl] - boog lyrics
- frostedglasses - magayon lyrics
- denan pro - lnc lyrics
- hally napoli - 1st chapter lyrics
- joe aaron reid - when i first saw you lyrics
- kxstutz - how could i forget lyrics
- pedrem - eu vou estar aqui lyrics
- 羊文学 (hitsujibungaku) - コーリング (calling) lyrics