azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

ጎሳዬ ተስፋዬ (gossaye tesfaye) - ልቧን አልፎ (libuan alfo) lyrics

Loading...

አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ
አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ
አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ
አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ
ምነው ብወዳት የሷን ፍቅር የሚያህል ፍቅር ብሰጣት
እላለሁ እላለሁ
ምነው ብወዳት ያለምንም ቅሬታ ልቤን ብሰጣት
እላለሁ እላለሁ
ግን ብዬ ግን ብዬ ምን እንደሆን አላውቅም ዛሬ
(ሞክሬ) አልቻልኩም (ሞክሬ) እኔ አልቻልኩም
ሞክሬም ሞክሬም ከሆንሽልኝ እሩብ አልሆንኩም
(ሞክሬ) አልቻልኩም (ሞክሬ) እኔ አልቻልኩም
እስኪ ምን ሆኜ ነው ያቃተኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
ይመስል የተሻለ የማገኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
እኔን ያንቺ ማረግ ያቃተኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
ማነው ብኩን አርጎ ያስቀረኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
እልፍ እንደሞላ የዓይን አዋጅ ሆኖ
ያንቺ አይነት የሚገኝ የትም
የኔ እንዲ መሆን ለምን እንደሆን
እንጃልኝ ገብቶኝ አያውቅም
ለዓይን እስኪነበብ የፍቅርሽ ፊደል
ተገልፆ በዓይኖቼ እያየው
የቱንም ያህል ልወድሽ ብጥር
አልቻልኩም ይቅርታ አዝናለሁ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ገና ተፅፎ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ያየዋል ዓይኔ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ፍቅር በዓይኗ ፅፎ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ያየዋል ዓይኔ

ምነው ብወዳት ለኔ ደስታ የማትከፍለው የማቶነው የላት
እላለሁ እላለሁ
ምነው ብወዳት እስካገኛት ብጓጓ ብናፍቃት
እላለሁ እላለሁ
ከሚገባሽ በታች ቢሆን ልቤ የሰጠሽ ቦታ
(ሞክሬ) አልቻልኩም (ሞክሬ) እኔ አልቻልኩም
ከፍቅር የተሰራሽ መሆንሽን አይክድም ላፍታ
(ሞክሬ) አልቻልኩም (ሞክሬ) እኔ አልቻልኩም
እስኪ ምን ሆኜ ነው ያቃተኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
ይመስል የተሻለ የማገኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
እኔን ያንቺ ማረግ ያቃተኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
ማነው ብኩን አርጎ ያስቀረኝ (ኦኦ ኦኦኦ)
እልፍ እንደሞላ የዓይን አዋጅ ሆኖ
ያንቺ አይነት የሚገኝ የትም
የኔ እንዲ መሆን ለምን እንደሆን
እንጃልኝ ገብቶኝ አያውቅም
ለዓይን እስኪነበብ የፍቅርሽ ፊደል
ተገልፆ በዓይኖቼ እያየው
የቱንም ያህል ልወድሽ ብጥር
አልቻልኩም ይቅርታ አዝናለሁ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ገና ተፅፎ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ያየዋል ዓይኔ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ)
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ያየዋል ዓይኔ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ገና ተፅፎ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ያየዋል ዓይኔ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ)
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ) ያየዋል ዓይኔ
(አልፎ ልቧን አልፎ ልቧን አልፎ)
(አልፎ) ል’ ልቧን አልፎ
(አልፎ) ል’ ልቧን አልፎ
(አልፎ)
(አልፎ)



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...