azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

rahel getu - hahu lyrics

Loading...

ሀሁ ለሉ ብዬ በመውደድ ስማር
እውቀቴን ገነባሁ ያንደበትህ ማማር
ሁል ጊዜህ አፍህ ላይ ልጣለው ጆሮዬን
ባንተ አለምን ሳውቃት ወደድኩት ኑሮዬን
ይሂው በአነጋገር በኑሮ በስዬ በስዬ
ታየሁ በሰዎች ፊት አስተዋይ መስዬ መስዬ
ዘንድሮ ተደነኩ በማፈልቀው ሃሳብ አይ ሃሳብ
ቁም ነገር አግኝቼ በአንደበት ስሳብ አይ ስሳብ
ሊቄ ነህ መምሬ ለፍቅር ጅማሬ
ፍቅርን ለማወቄ የኔታ ጠቢቤ

ልጅ ናት ይሉኝ ነበር ከበፊት የሚያቁኝ
ዛሬ አዋቂ አድርገውኝ በሰፊው ጠየቁኝ
ለሁሉም ስመልስ መች አፈርኩብህ
ከልቤ ነው እና የተማርኩብህ
ገልጸህ ያሳያኘኝ ሁሉንም እንድረዳ
ፊደሌ ሆነሃል የሂወቴ አቦጊዳ
በሃሳብ አሻራ ላይ ያሰነበትከኝ
ከቅኔው ሊቃወውንት ተርታ የከተኽኝ
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ

ፊደሌ ብልህ መች ይገልጽሃል
እንደ ሂዎቴ ድርሳን ልቤ ያነብሃል
ሀ ግእዝ ሁ ካዪብ እያልኩህ በስምህ
እንደ ዳዊቴ ነው የምደጋግምህ
ቀርቦ ለሚያደምጠው ንግግርህ ሲያምር
ሂዎትን ያቃናል ያንተ ቃል ሲያስተምር
ነብስን ትገራለህ ባደለህ አንደበት
አሁንም አሁንም ደጋግመህ አውራበት
እሮጬበታለው የልጅን መንገድ
ካሰቡት ያደርሳል ያወቀን መውደድ
በጥበብህ ስበህ ከልብህ ስትከተኝ
ጥሩ ሄጃለው ወይ ስትመለከተኝ?
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...