tedy afro - እቴጌ (etege) lyrics
ኧረ ባላውቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ ምድር ላይ ገና ዓለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሁሌም ለእመቤቴ
ኧረ ባላውቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ ምድር ላይ ገና ዓለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሁሌም ለእመቤቴ
ለጉድ አሳምሯት ምትኳ እንዳይገኝ
ጥሎኛል ከእጇ ላይ እንዳሻት ታድርገኝ
በምን ይኮነናል ቢጠየቅስ ነፍሷ
የሸጠኝ ፍቅር ነው የገዛቺኝ እሷ
ለጉድ አሳምሯት ምትኳ እንዳይገኝ
ጥሎኛል ከእጇ ላይ እንዳሻት ታድርገኝ
በምን ይኮነናል ቢጠየቅስ ነፍሷ
የሸጠኝ ፍቅር ነው የገዛቺኝ እሷ
እንደለፋበት በወንድነቴ
አቤት እያልኩኝ ለእመቤቴ
የፍቅር ንጉስ የፍቅር ጌታ
እኔ ሎሌ ነኝ እሷ በላታ
ከረታኝ ፍቅርሽ ምን አደርጋለሁ
አላለልኝም እችለዋለው
አላለልኝም እችለዋለው
አላለልኝም እችለዋለው
ኧረ ባላውቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ ምድር ላይ ገና ዓለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሁሌም ለእመቤቴ
ኧረ ባላውቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ ምድር ላይ ገና ዓለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሁሌም ለእመቤቴ
ሀቢ ነው የፍቅር ልብ ነው ዙፋን
እንዲህ አይደለም ወይ ወደው ሲታመኑ
ሹም እንዳዘዘው ሰው አጎንብሼ መሬት
ስትጠራኝ አቤት ነው ስትልከኝ ወዴት
ተጣሩ እቴኔ አቤት በልአሽከር
ወደህ በገባህ አትከራከር
ወዶ ለገባ በቴጌ ቤት
አዲስ አደለም አቤት ማለት
ክብሬ ተነካ ስትል ማረጌ
አቤት ብቻ ነው ሲጣሩ እቴጌ
አላላልኝም እችለዋለሁ
አላላልኝም እችለዋለሁ
እቴጌ (አቤት አቤት)
እቴጌ (አቤት አቤት)
እቴጌ እቴጌ
እቴጌ እቴጌ
Random Lyrics
- josuelson sabatinelli - volta lá lyrics
- greentea peng - saturn lyrics
- the cast of rupaul’s drag race uk - break up bye bye - filth harmony version lyrics
- preto & branco - energia (noite) lyrics
- klithe893 - xaxa&fiji lyrics
- operación triunfo 2017 - lady marmalade lyrics
- glue70 - til you say lyrics
- yö - tiedän liikaa elämästä lyrics
- diesilly - high lyrics
- juntino - confetti lyrics