
yamlu molla feat. hanna girma - ere enja lyrics
ከፍቶኝ ዛሬ ዋለ ሆ! ምንድነው ሚስጥሩ
ወና መና ሲሆን ሞቅ ብሎ መንደሩ
ለልቤ ደስታ ሆ! ሆነ ባይተዋሩ
ያኔ እንደ ወዳጅ አሄ! እንዳልተፋቀሩ
ስንቴ ስልኬን አየሁ ኦ! በሰበብ ባስባቡ
እንዲ እንደሚያረገኝ ግን ስረዳው ′ባግባቡ
ለካ ተይዣለሁ ኦ! በመውደድ መረቡ
ቀስ ብለህ ያረከው እህ! ገባልኝ ሸረቡ
(ተረታ) አንተዬ ሰሞኑ
(ተረታ) እንዲ መጨከኑ
(ተረታ) ፍቅር አሲዞ
(ተረታ) ኸረ የለም ጉዞ
(ተረታ) አንተዬ ሰሞኑ
(ተረታ) እንዲ መጨከኑ
(ተረታ) ፍቅር አሲዞ
(ተረታ) የምን ነው ጉዞ
ኸረ እንጃ ‘ኔ ኸረ እንጃ ′ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር ልጣ ወኔ
ኸረ እንጃ ‘ኔ ኸረ እንጃ ‘ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር አጣሁ ወኔ
ረጋ ለዘብ ብሎ ሆ! ተሳካ ውጥኑ
ለልቤ የተበጀው አሄ! መች ያዘው ወሰኑ
እኔን ከ′ኔ አጣልቶ ሆነ ′ሱ ሸምጋዩ
አቆመኝ ከሸንጎ ከአደባባዩ
(ተረታ) አንተዬ ሰሞኑ
(ተረታ) እንዲ መጨከኑ
(ተረታ) ፍቅር አሲዞ
(ተረታ) ኸረ የለም ጉዞ
(ተረታ) አንተዬ ሰሞኑ
(ተረታ) እንዲ መጨከኑ
(ተረታ) ፍቅር አሲዞ
(ተረታ) የምን ነው ጉዞ
ኸረ እንጃ ‘ኔ ኸረ እንጃ ′ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር ልጣ ወኔ
ኸረ እንጃ ‘ኔ ኸረ እንጃ ′ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር አጣሁ ወኔ
ፍቅር ባረገጠው በብለሃት መ’ቶ
እውስጤ ዘለቀ ለልቤ ተስማምቶ
እግር ባልበዛበት ተጠንቅቆ መ′ቶ
እውስጤ ሲገባ አሄ+ሄ! መቼ እሱ ወትውቶ
(ተረታ) አንተዬ ሰሞኑ
(ተረታ) እንዲ መጨከኑ
(ተረታ) ፍቅር አሲዞ
(ተረታ) የምን ነው ጉዞ
ኸረ እንጃ ‘ኔ ኸረ እንጃ ‘ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር ልጣ ወኔ
ኸረ እንጃ ′ኔ ኸረ እንጃ ′ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር አጣሁ ወኔ
ኸረ እንጃ ‘ኔ ኸረ እንጃ ′ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር ልጣ ወኔ
ኸረ እንጃ ‘ኔ ኸረ እንጃ ′ኔ
አልሆን አለኝ ሳጣህ ጎኔ
ኸረ ወይኔ ልጅት ወይኔ
ባንተ ነገር አጣሁ ወኔ
Random Lyrics
- candlebox - all down hill from here lyrics
- d3athv1b3z - tutu lyrics
- matthew spencer - antithesis lyrics
- yung gravy & trippythakid - steppin on the beat lyrics
- tünzalə ağayeva - gəlmədin lyrics
- karan aujla - it ain't legal lyrics
- grisha urgant - ночной каприз (night caprice) lyrics
- nakele - enemies lyrics
- smoking popes - can't find it [1997 version] lyrics
- visoldin - индифферентно (indifferent) lyrics