azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

abenet agonafer – chuh chuh lyrics

Loading...

ኑሮ እንዴት አድርጎሻል
ኧረ እንዴትስ ይዞሻል
አንቺ እንደድሮው ነሽ ወይ
ወይ ተለውጠሻል
ኧረ እንዴት አስችሎሻል
ኧረ እንዴትስ ይዞሻል
ደልቶሽ ነው ወይ ኑሮው
ወይንስ ተጎድተሻል
አልሰማም እኔስ ስላንቺ ናፍቄያለሁ
እንዲህ ነው ብሎ የሚነግረኝ አጥቻለሁ
አልሰማም እኔስ ቢከፋሽም ቢደላሽ
በህይወት ኑሪ ክፉ አኝቺን እንዳይነካሽ
ትዝታሽ ተጭኖኛል
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
ኧረ እንዴት ይሻለኛል
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
ባ’ይኔ ላይ ስትመጪ
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
ምሆነው ይጠፋኛል
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
ትነግሪኝ ነበር ሀዘን ደስታውን
ያንቺንም የኔንም ያ’ካባቢውን
ትነግሪኝ ነበረ ለኔ ያለሽን
ስንቅ እንዲሆነኝ ደግ ሃሳብሽን
ይሆን ወይ ስራው አዲሱ ኑሮ
አንቺን ያጠፋሽ ድንገት ዘንድሮ
ይሆን ወይ ትዳር ክፉ አባወራ
ያቆራረጠሽ ከወዳጅ ጋራ
የት ስቀሻል የት አዝነሻል
የት ውለሻል የትስ አድረሻል
ያንቺ ነገር አልሆን አለኝ
አለሁ በይኝ ተይ እንዲቀለኝ
ኑሮ እንዴት አድርጎሻል
ኧረ እንዴትስ ይዞሻል
አንቺ እንደድሮው ነሽ ወይ
ወይ ተለውጠሻል
ኧረ እንዴት አስችሎሻል
ኧረ እንዴትስ ይዞሻል
ደልቶሽ ነው ወይ ኑሮው
ወይንስ ተጎድተሻል
አልሰማም እኔስ ማንን እጠይቃለሁ
ከወዳጅ ዘመድ ታውቂያለሽ እርቂያለሁ
አልሰማም እኔስ ክፉ እንኳን ቢደርስብሽ
ያስጨንቀኛል ወዳጄ እባክሽ የት ነሽ
ሲከፋኝ አፅናኝ ሳጣ
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
የዛሬው ግን ከብዶኛል
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
ደጉን ቀን ሳስታውሰው
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
የሆንነው ይገርመኛል
ጩህ ጩህ ጩህ ጩህ ይለኛል
ትነግሪኝ ነበር ሀዘን ደስታውን
ያንቺንም የኔንም ያ’ካባቢውን
ትነግሪኝ ነበረ ለኔ ያለሽን
ስንቅ እንዲሆነኝ ደግ ሃሳብሽን
ይሆን ወይ ስራው አዲሱ ኑሮ
አንቺን ያጠፋሽ ድንገት ዘንድሮ
ይሆን ወይ ትዳር ክፉ አባወራ
ያቆራረጠሽ ከወዳጅ ጋራ
የት ስቀሻል የት አዝነሻል
የት ውለሻል የትስ አድረሻል
ያንቺ ነገር አልሆን አለኝ
አለሁ በይኝ ተይ እንዲቀለኝ
ትነግሪኝ ነበር ሀዘን ደስታውን
ያንቺንም የኔንም ያ’ካባቢውን
ትነግሪኝ ነበረ ለኔ ያለሽን
ስንቅ እንዲሆነኝ ደግ ሃሳብሽን
ይሆን ወይ ስራው አዲሱ ኑሮ
አንቺን ያጠፋሽ ድንገት ዘንድሮ
ይሆን ወይ ትዳር ክፉ አባወራ
ያቆራረጠሽ ከወዳጅ ጋራ



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...