azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

dawit cherent – edmea lyrics

Loading...

በድንግዝግዝ አለም ብልጭታ አለ ግን ሩቅ ይመስላል
ሊይዝ ሊጨብጠው መንገድ የጀመረውን ሰው እውር ይመራዋል
አልችልም እራስን አጥቶ መኖር እራስን ጠልቶ ጠፋለው
አልችልም ተቀያይሞ መኖር አታሎ እፈራለው

ጨለማ ነው
ጨለማ ነው

እድሜ ተቆጥሮ ቢያልቅ ጊዜው
ዘመናት ቢያልፉ እንደወትሮው
አይቀርም እራስን ማየት ወደውስጥ
ያኔ ይቆጫል ሳይኖሩ መሞት

ዛሬ ታይቶ ነገ እንደሚጠፋ እንደ እንፋሎት ነው
ተው ያዝ እውነትን እንዳጥል ተንከባከበው
ማየትን እመርጣለው ወደውስጥ አሻግሬ ላገኘው
ፋኖሱ ሊጠፋ ቢል ዘይቱ ተንጠባጥቦ ሊያልቀው

ግን እጓዛለው
ግን እጓዛለው

እድሜ ተቆጥሮ ቢያልቅ ጊዜው
ዘመናት ቢያልፉ እንደወትሮው
አይቀርም እራስን ማየት ወደውስጥ
ያኔ ይቆጫል ሳይኖሩ መሞት

ተጉዤ ተጉዤ ደረስኩ መጨረሻ
ያየሗት ብልጭታ ሆነች ጨለማ
ሙጥጥ ብሎ አለቀ የያዝኩት እምነቴ
በሩ እንደተዘጋ ሞትን ፈርቼ

እድሜ ተቆጥሮ ቢያልቅ ጊዜው
ዘመናት ቢያልፉ እንደወትሮው
አይቀርም እራስን ማየት ወደውስጥ
ያኔ ይቆጫል ሳይኖሩ መሞት



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...