jacky gosee – hilm ayew lyrics
Loading...
ጎኔ አላረፈ አይኔም አልከዳኝ
ይገርማል ውዴ ደርሶ የገጠመኝ
ህልም አየው ውዴ ህልም አየውባንቺ የምዳኘው ህልም አየው(2)
እስኪ ገምቺው ምን ይመስልሻል
ለኔ የታየው ታይቶሽ ይሆናል
በሰፊው ግዛት ፍቅርን አየሁት
በሰፊው ግዛት ደምቆ አገኘሁት
ልቤ ሰምሮለት አፍቃሪነቱ
ባሴት ተሞልቶ ጓዳና ቤቱ
ስትኖሪ ለኔ ሲያኖረኝ ላንቺው
ደርሶ ማለሜን በይ እስኪ ፍቺው
ፍቺልኝ እስኪ ፍቺልኝ ህልሜን ንገሪኝ(2)
እኔን ንብ አርጎኝ አንቺን አበባ
ታየኝ በህልሜ ቤትሽ ስገባ
ከልብሽ አደይ ፍቅርን ቀስሜ
የልብሽን ማር ሰራው በህልሜ
ከፍቅር ገዳም ደውል ሲሰማ
ንጋት ሲያበስር ወፎች በዜማ
አዲስ ቀን አየው ካንቺ ጋር ውዴ
እስኪ ፍቺልኝ ሲሳይ ነው እንዴ
ፍቺልኝ እስኪ ህልሜን ንገሪኝ
ፍቺልኝ እስኪ ፍቺልኛ እንዲ ነው በይኝ
Random Lyrics
- tede – 199ii lyrics
- tede – kochanie lyrics
- tede – fryderyk_chopin lyrics
- aaron west and the roaring twenties – my favourite chords lyrics
- ed sheeran – i don’t care lyrics
- step back j – i like lyrics
- janella salvador – kapag tumibok ang puso (duet with marlo mortel) lyrics
- marcel daimon – miel lyrics
- tede – młody hugh hefner lyrics
- amrit maan – jatt fattey chakk lyrics