kemi – bete lyrics
ቤ ቴ ቤ ቴ በጣም ቆሽሸሻል
ከላይ ብቻ እንጂ ውስጥሽ ፈርስዋል
ቤ ቴ ቤ ቴ በጣም ያሳስባል
ከላይ እንጂ ዉስጥሽን ማን አይትዋል
አንቺ ነሽ ምክንያቱ ይህ አለም አለመጥፋቱ
ብርሀን ስለሆንሽለት ሆኖለታል መሰንበት
ጨው ባትሆኚ ኖሮ አልቆለት ነበር ድሮ
የእግዚአብሄር ወኪል በምድር ይጠበቅብሻል መኖር
ያለሽን ጉድፍ ተይና ለሰው መኖር ጀምሪና ሰውን ከአምላኩ አስታርቂና ኢየሱስን አሳዪና
እሱ ለሰው ሁሉ ይራራል የመዳንን እውቀት ይሰጣል ከሞትም ቢሆን ያድናል ኢየሱስ ያድናል
በበግ በረት ብዙ ዶሮ ብዙ ጫጩት በጉረኖ አወይ ዛሬ አወይ ድሮ ያለቦታው ብዙ ሮሮ
የተገባው ባልተገባው ያለተገባው በተገባው ይህም ያም ግን ግራ ገባው ማን ይደልድል ማን ያግባባው
ብዙ ወሬ ጥቂት ድርጊት መንፈሳዊ ለአለም ጡዘት ባስተሳሰብ ብዙ ግጭት ማን ያድነን ከዚህ ዉጥረት
ወደሽ ስትታዪ ምድራዊ ምቾትን መሰብሰብ ጥሪትን ማካበት ትእቢትን
ይህን የሚቃወም አባረሽ እውነትን ልጆችሽ እንደባይተዋር ሲጭሩ ክብሪትን
ሊያወድሙሽ ሲነሱ ጠላት እንደሆኑ ምንም አልመሰለሽ ተውሻቸው እነሱን
አንድም ሀላፊነት አልሰማሽ ብሎ ሀላፊነት ሰጪው ከውጪ እሱ ቆሞ
ሊገባ ያንኩዋኩዋል ትከፍቺ እንደሆን ዘንድሮ ያባረርሺዉን ልጀች ሁሉ በጆቹ ይዞ
አይ አንቺማ እግሮችሽን ሰቅለሻል ቲቪሽን ከፍተሻል ጋቢሽን ለብሰሻል ሞቅ ሞቅ ብሎሻል
ከሰል አቀጣጥለሽ ላብ በላብ ሆነሻል ግን አልታወቀሽም ተባይ አፍርተሻል ቢደውል ቢያንኩዋንኩዋ
አልሰማ ብለሻል ከሱ ሰላም ይልቅ ሁካታን መርጠሻል ከእውነት ቃል ይልቅም ሽንገላን ወደሻል
ከቶ አልገባሽም ቀን ግን ቆርጦልሻል አሁንም ግን እሱ በፍቅር ይጣራል ከሁሉ አስበልጦ ዛሬም ይዎድሻል
ቤ ቴ ቤ ቴ በጣም ቆሽሸሻል
ከላይ ብቻ እንጂ ውስጥሽ ፈርስዋል
ቤ ቴ ቤ ቴ በጣም ያሳስባል
ከላይ እንጂ ዉስጥሽን ማን አይትዋል
Random Lyrics
- pbrezzy – drug lyrics
- brytiago – aprendi a amar lyrics
- los acosta – es tan terrible lyrics
- dreamdoll – team dream lyrics
- влад соколовский – вопреки всему lyrics
- dreamdoll – splish splash lyrics
- basenji – about you lyrics
- frozen crown – in the dark lyrics
- vendredi sur mer – j’aimerais lyrics
- broods – every time you go lyrics