azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

rophnan – yidres lyrics

Loading...

ይድረስ ለምወድሽ እጅግ ለምታምሪው
ይድረስ ላይኔ ቆንጆ ይህን ለምትሰሚው
የውስጤን በደብዳቤ እንዲህ ብዬ ፃፍኩት

ግን ፖስታውን ትቼ በዜማዬ አሸግኩት
ከአልማዝ ከእንቁ በላይ መልእክቴ ይበልጣል
ወረቀት ተቀዳጅ ነው እንዴት ይታመናል?
ስለዚህ ደብዳቤዬን ፅፌ እንደጨረስኩት
ፖስታውን ተውኩና በሙዚቃው ላኩት

ሰው የለም እንዳንቺ ልቤ የወደደው
ሲነጋም ሲመሽም አንቺን ነው ‘ማስበው
እውነቱን ሳልናገር ሁሌ ከምትርቂኝ
እንግዲህ እጠብቃለሁ ምን እንደምትይኝ ኤይ

(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)

ይድረስ ለኔ ቆንጆ ይድረስ ለኔ ውብ
ሳይሽ ዋልኩኝና አደርኩኝ ሳልም
ማየቱስ ምን ሊያደርግልኝ ማለሙም ትርፍ የለው
ባገኝሽ ነው እንጂ ልቤን የእውነት ደስ የሚለው
እንዳልኩሽ መልእክቴ ከአልማዝ ይበልጣል
የፍቅር ቃላት በምን ዋጋው ይተመናል?
ስለዚህ ደብዳቤዬን ፅፌ እንደጨረኩት
ፖስታውን ተውኩና በሙዚቃው ላኩት

ሰው የለም እንዳንቺ ልቤ የወደደው
ሲነጋም ሲመሽም አንቺን ነው ‘ማስበው
እውነቱን ሳልናገር ሁሌ ከምትርቂኝ
እንግዲህ እጠብቃለሁ ምን እንደምትይኝ ኤይ

(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)

(ና+ና+ና)
አማሌሌሌሌሌሌሌ ናናዬ (ና+ና+ና)
መልሱን ልከሽልኝ ልዳነው ከ ስቃዬ (ና+ና+ና)
ሽኮሪናናናናናናናና ናናዬ (ና+ና+ና)
ደብዳቤዬን ላኩት በዚህ ሙዚቃዬ (ና+ና+ና)

ሰው የለም እንዳንቺ ልቤ የወደደው
ሲነጋም ሲመሽም አንቺን ነው ማስበው
እውነቱን ሳልናገር ሁሌ ከምትርቂኝ
እንግዲህ እጠብቃለሁ ምን እንደምትይኝ ኤይ

(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)
(ኤይ+ኤይ+ኤይ)

እንግዲህ እጠብቃለሁ ምን እንደምትይኝ ኤይ



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...