azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

tekeste getnet – alsham lyrics

Loading...

ትዝ ይለኛል
ማንም አልነበረም ከጎኔ
ትላንት በበረሃ

ትዝ ይለኛል
አንተ ነህ ኃይሌን ያደስክልኝ
ሆነህ የህይወት ውሃ
ትዝ ይለኛል
የዛሬውን አይተህ ልጅ ሳለሁ
ለክፉ እንዳልተውከኝ
ትዝ ይለኛል
አወን አልረሳውም ጌታዬ
ክበር ያከበርከኝ

አልረሳውም

ያንዳንዱ ቅንነት ቀን እስከሚወጣ
ያንዳንዱ +++++ ዘመን እስኪመጣ
ለካ ሲያስመስል ነው
እንዲያ የነበረ
ሲያገኝ መስሎኝ ነበር ፀባይ የቀየረ

አድነኝ ባሪያህን አድነኝ
አድነኝ እንዲህ ካለው ነገር
ዘመኔ ይለፍ በቤትህ
ጌታዬ አንተን በማክበር
አድነኝ ልጅህን አድነኝ
አድነኝ እንዲህ ካለው ነገር
ዘመኔ ይጠቅለልልኝ
ጌታዬ አንተን በማክበር

ከቅኖቹ ጋራ ቀና ትሆናለህ
ከጠማማ ጋራ አንተም እንደዚያው ነህ
የዋሁን ከአንበሳ ጉድጓድ ስታተርፈው
ጠማማውን ንጉስ በትል አስበላኸው
መነሻ ሁሉ ዘንግቶ በትዕቢት ለተወጠረ
ቢያስተውል ቢበጀው ነበር+
ያላንተ
ማንስ ከበረ
የሰጠኸው ካንተ ካራቀው መንገዱ ላይ ትቆማለህ
ሚመካ ሚኮራበትን ከጁ ላይ ትበትናለህ
ለከበረ ነገር ነበር የጠራኸው
በጥቂቱ ረክቶ ትዕቢት ባይወጥረው
ካሰብክለት ክብር ስንቱ ሰው ጎደለ
ቅንነቱን ጥሎ ባልዋልክበት ዋለ

አድነኝ እኔንስ አድነኝ
(አድነኝ)
አድነኝ እንዲህ ካለው ነገር
ዘመኔ ይለቅ በቤትህ
(አቤቱ)
ጌታዬ አንተን በማክበር
አድነኝ ልጅህን አድነኝ
(አድነኝ)
አድነኝ እንዲህ ካለው ነገር
ዘመኔ ይደምደምልኝ
(አቤቱ)
ጌታዬ አንተን በማክበር
አድነኝ እኔንስ አድነኝ
(አድነኝ)
አድነኝ እንዲህ ካለው ነገር
ዘመኔ ይለቅ በቤትህ
ጌታዬ አንተን በማክበር
(አድነኝ)
አድነኝ ልጅህን አድነኝ
(አድነኝ)
አድነኝ እንዲህ ካለው ነገር
(አድነኝ)
ዘመኔ ይደምደምልኝ
(አድነኝ)
ጌታዬ አንተን በማክበር
(አድነኝ)
ጌታዬ አንተን በማክበር
(አድነኝ)



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...