azlyrics.biz
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

dawit cherent – zaf lyrics

Loading...

ተስፋ ተጥሎበት የት ይደርሳል ተብሎ
ኀላፊ አግዳሚው በርሱ ተገርሞ
ባፈራው ቅርንጫፍ ስንቱን አስጠልሎ

ይኖር ነበረ የኖረ መስሎ

ግን ተቆረጠ በሰዎች እጅ ወደቀ
ተስፋ እንዳይኖረውም ተሰነጠቀ
መልሶ እንዳይበቅል ደግሞ እንዳይሆን ጥላ
በቅርንጫፎቹ መጥረቢያ ተሰራ

አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ

ግን ደግሞ ይነሳል አይሞትም እሱ
ያቆጠቁጣል ከሞተው ክፍሉ
መልሶ ይመጣል ውሀን አሽቶ
አብዝቶ ያፈራል ከቀድሞ አብልጦ

መውደቅ እንዳለ አለ ደግሞ መነሳት
ተስፋ አጥቶ ደግሞ ማግኘት መልሳ ተስፋን
አይቀርም ደርቆ አለ መልሶ ማፍራት
ዛሬ የጠፋው ነገ ደግሞ ይበራል

ሰዎች ቢሉት የሞተ የተላቀቀም ቢመስል ከፍጥረት ጎራ (ጎራ)
አይመለስ ብለው ለዘላለም አሸልቧል በቃ ለይቷል
ይሰማል መንፈሱ በህይወት ጎዳና ስሙን ሰምቶ ይወጣል (ጎበዝ ና ውጣ)
ዳግም አንሰራርቶ ሙታንን ተላቆ (መጣ) ከህያዋን መንደር
ራሱን ሰቶ ለህይወትም ቃና
አሽብርቆ ይታይ የለ ገና
አልጨረሰም አለው አለው ሌላ
በዝቶለታ አለው ገና ገና
ቆሞ ይሄዳል እንዳዲስ ነው ሌላ
ከሞተበት ክፍል መቃብሩ ተከፍቶ ይወጣልና

አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ

አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ



Random Lyrics

HOT LYRICS

Loading...